Welcome!
If you are looking for a breakthrough in teaching Ethiopian alphabets, the Amharic language & early fundamental science for your kids, then you are in the right place.
Shipping to all destinations!Our widely acclaimed Ethiopian alphabet teaching DVDs, Vol. I & Vol. II, have been on the market since Dec. 2010 & April 2012, respectively. Both DVDs have been, and are still being distributed to all destinations around the world. They are available to buy here from our website.
Our remarkable Science teaching DVD has been released on June 22, 2013. The first language DVD (Vol. 1) is fully animated and it teaches:
The second language DVD, titled "Kids' Feast of Ethiopic & the Ethiopian Lingua franca" contains the following:-
The fully animated Science DVD (Vol. I), narrated in both English & Amharic with 3 different voices, teaches about the following vital organs & their functions in very simple terms using superb visuals, audio & beautiful songs that are reinforcing the lessons:
Science Vol 1 is divided in to 2 parts, Part 1, which is available now, & Part 2, which will be released in the following weeks. The Science DVD (Vol. 1 Part 1) includes all lessons about the first 4 major internal organs, namely, the skeleton, the brain, the lungs and the heart. It is available to order from our website. The Science DVD ( Vol. 1 Part 2) includes lessons about the liver, the kidneys, the muscles, the skin and the five sense organs. All the 3 DVDs, language Vol. 1 and Vol. 2, and Science Vol. I(P1), are sold only on our website. Please don’t forget to choose the name of the item & Vol. No. from the options menu when you place your order. You only pay for one shipping and handling when you order all the 3 DVDs together for a saving or $ 14 dollars, and any 2 DVDs together, for a saving of about $7 dollars. Ethiopian syllabic alphabets are used by Amharic, the official language of Ethiopia, and many more languages spoken in Ethiopia and elsewhere. Amharic alone is spoken by several tens of millions of people. It is the second widely spoken Semitic language in the world. |
Language Vol 1 (ወይም ቋንቋ ቁጥር ፩ (1)) ዲቪዲ የሚከተሉትን ይዟል፦
Language Vol 2 (ወይም ቋንቋ ቁጥር ፪ (2)) ዲቪዲ የሚከተሉትን ይዟል፡-
Science Vol 1 (ሳይንስ ቁጥር ፩) ስለሚከተሉት የሰውነት ክፍሎች ትምህርት ይዟል፦
የሳይንስ ዲቪዲው በሁለት ክፍሎች የተከፈለ ነው። አሁን በገበያ ላይ የዋለው ክፍል 1 (P1) ሲሆን በቅርቡ ክፍል 2 (P2) ይለቀቃል። ክፍል 1 ስለመጀመሪያዎቹ 4 ዋና ዋና የሰውነት ክፍሎች (አእምሮ፣ ሥርዓተ አጽም፣ ሳምባ እና ልብ) ትምህርት የያዘ ነው። ክፍል ሁለት ደግሞ ቀጥሎ የሚገኙትን 4 ዋና ዋና የሰውነት ክፍሎች (ጉበት፣ ኩላሊት፣ ጡንቻ፣ ቆዳ) እና የስሜት ህዋሳትን በማጠቃለል ያስተምራል። ዲቪዲዎችን በምታዙበት ጊዜ የምትገዙት የቋንቋ ዲቪዲ ከሆነ ከምርጫዎቹ ውስጥ Language Volume 1 ወይም Language Volume 2፤ ሁለቱን የምታዝዙ ከሆነ ደግሞ Language Vol. 1 & 2 የሚሉትን ምረጡ። የሳይንሱን መማሪያ ዲቪዲ የምታዙ ከሆነ Science Vol 1 (P1) የሚለውን ምረጡ። የትኛውንም ሁለቱን ዲቪዲዎች በአንድ ጊዜ በምታዙ ጊዜ የምትከፍሉት የአንዱን ብቻ መላኪያ ስለሆነ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ $7 ታተርፋላችሁ። ሦስቱንም ዲቪዲዎች በምታዙ ጊዜ (All 3 DVDs የሚለውን ምረጡ) የምትከፍሉት የአንዱን ብቻ መላኪያ ስለሆነ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ $14 ታተርፋላችሁ። በብዛት በቤተክርስቲያን ማዘዝ ለምትፈልጉ የዋጋ ቅናሽ ስላለን በኢሜል (fhlproduction@yahoo.com) ወይም በስልክ ቁጥር (403) 764-9184 ደውላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ። "ሞክሼ" ሆሄያት ለምን ያስፈልጋሉ? አጠቃቀማቸውስ?በተደጋጋሚ ከሚደርሱን ጥያቄዎች አንዱ "ሞክሼ" ሆሄያት (ሀ፣ ሐ፣ ኀ / ሰ፣ሠ / አ፣ዐ / ጸ፣ፀ) ለምን ያስፈልጋሉ? አጠቃቀማቸውስ? የሚል ነው። ጉዳዩ ሰፊ ቢሆንም በአጭሩ እንደሚከተለው መልስ እናቀርባለን። Read more...
Why Ethiopic has 3 Ha's (ሀ/ሐ/ኀ), 2 Sa's (ሰ/ሠ), 2 A's (አ/ዐ), 2 Tsa's (ጸ/ፀ)?This is one of the most frequent questions we receive. It will be addressed briefly below. Read more...
Links:- |
q ቁጥር ፩ ዲቪዲ ከተዘጋጀ በኋላ የተለያየ የዕድሜ ክልል ባላቸው በርካታ ልጆች ላይ ተሞክሮ የተገኘው ውጤት የሚያስደንቅ ነው። በጥናቱ የተካተቱት ልጆች በሙሉ የመጀመሪያ (ግእዝ) ፊደላትን በሁለት ሳምንት ውስጥ ጠቅላላ የፈደል ዘሮችን ደግሞ በሦስት ወር አጠናቀው ሊያውቁ በቅተዋል።
|
q ቋንቋን ለልጆች ማውረስ አገርን ማውረስ ነው። አገር ማለት መልክዓምድሩ፣ በውስጡ ያለው ሀብትና አየር ንብረቱ ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ሕዝቡ ነው። አንድን ሕዝብ ከሌላው የሚለዩት ማንነቱ፣ እምነቱ፣ ባህሉ፣ ታሪኩና ቅርሱ ናቸው። ቋንቋን ማውረስ ይህን ባህል ማውረስ ነው። ቋንቋን ማውረስ እምነትን ማውረስ ነው። ቋንቋን ማውረስ ታሪክን ማውረስ ነው። ቋንቋን ማውረስ ማንነትን፣ ቅርስንና ሌሎችንም አገርን አገር የሚያደርጉትን እሴቶች ሁሉ ለልጆች ማውረስ ነው። እነዚህ እሴቶች የሌሉት ሰው የተሟላ ሊሆን አይችልም።
|
አማርኛ እና ሌሎች የአፍሪካ ቋንቋዎች በአሜሪካ'Slate' የተባለ መጽሔት የአሜሪካንን የሕዝብ ቆጠራ እንደመረጃ አድርጎ በድረ-ገጹ ባወጣው ዘገባ በስምንቱ የአሜሪካ ግዛቶች (States) - ካሊፎርኒያ (California)፣ ኔቫዳ (Nevada)፣ ኮሎራዶ (Colorado)፣ ኒው ሜክሲኮ (New Mexico)፣ ደቡብ ዳኮታ (South Dakota)፣ ዋሽንግተን (Washington)፣ ምዕራብ ቨርጂኒያ (West Virginia) እና ቨርጂኒያ (Virginia) - ከአፍሪካ ቋንቋዎች መካከል በቀዳሚነት በስፋት የሚነገረው የአማርኛ ቋንቋ እንደሆነ በካርታ (US Map) አስደግፎ አስነብቧል። በሌሎች ግዛቶች ከአማርኛ በበለጠ እንደሚነገሩ ሆነው ሆኖም በዘገባው እንደአንድ ቋንቋ የተጠቀሱት ሦስት ቋንቋዎች (Kru, Ibo & Yoruba) በአንድነት ከመሆናቸውም በላይ እነዚህ ቋንቋዎች በስድስት የአፍሪካ አገሮች (ናይጀሪያ፣ ቤኒን፣ ላይቤሪያ፣ አይቮሪኮስት፣ ቡርኪናፋሶ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ) የሚነገሩ ናቸው። እነዚህ ሦስት ቋንቋዎች እንደአንድ መታየታቸው ቀርቶ እንደአማርኛ ቋንቋ በየራሳቸው ብቻ ብቻቸውን ከታዩ ከአፍሪካ ቋንቋዎች መካከል የአማርኛ ቋንቋ ምናልባትም በሌሎች ተጨማሪ የአሜሪካ ግዛቶች (እንደምሳሌ ቴክሳስ፣ ፍሎሪዳ፣ ፔልሲልቬንያ፣ ኒውዮርክ…) በቀዳሚነት በስፋት እንደሚነገር መገመት ይቻላል።
|
ይህን መረጃ እንደእውነተኛ እና አስተማማኝ መረጃ ልንቀበለው ከቻልን ይህ በጣም ጥሩ ነገር ነው። ምክንያቱም ይህ መሆኑ ቀስ በቀስ ለኢትዮጵያውያን ሌሎችንም ጥቅሞች የሚያስከትል በመሆኑ ነው። የአማርኛ ቋንቋ በዋሽንግተን ዲሲ (Washington, DC) ተጨማሪ የሥራ ቋንቋ ለመሆን መብቃቱን እንደቅርብ ምስክር ማቅረብ ይቻላል። በሂደት እንደ ማንደሪን (Mandarin) እና ስፓኒሽ (Spanish) ቋንቋዎች አማርኛም በመደበኛ ትምህርት ቤቶች ከሌሎች ትምህርቶች እኩል ጎን ለጎን መሰጠት እንዲጀምር መንገድ ይከፍታል። ሌሎችም በርካታ ጥቅሞች ይኖሩታል። ይሁን እንጂ ይህ ውጤት ዘላቂ እንዲሆንና አማርኛ ቋንቋም እያደገና እየሰፋ ይሄድ ዘንድ ቋንቋውን ሳንታክት ለልጆቻችን ማስተላለፍ ይጠበቅብናል። ያንን እስካላደረግን ድረስ ልጆቻችንን በቋንቋው እንዳይጠቀሙ በማድረግ ከመጉዳታችንም በላይ ይህንንም ውጤት ቢበዛ ከአንድ ትውልድ በላይ ማቆየት አንችልም። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን በጠቅላላ ተጎጂ የሚያደርግ ይሆናል። ለዚህ ነው ለልጆቻችን የአማርኛን ቋንቋ ማስተማር ስለታሪካቸው፣ ባሕላቸው፣ እምነታቸው፣ ማንነታቸው… እንዲያውቁ ከማድረግም በላይ ሌሎችም ጥቅሞች አሉት ለማለት የሚያስደፍረው።
ምንጭ፡ http://www.slate.com |