Welcome!
|
Volume I (1) (ወይም ቁጥር ፩ (1)) ዲቪዲ የሚከተሉትን ይዟል፦
አዲሱ Volume II (2) (ወይም ቁጥር ፪ (2)) ዲቪዲ ደግሞ የሚከተሉትን ይዟል፡-
ዲቪዲውን በምትገዙበት ጊዜ ከምርጫዎቹ ውስጥ Volume I (1) ወይም Volume II (2)፤ ሁለቱን የምታዝዙ ከሆነ ደግሞ Vol. 1(I) & Vol. 2 (II) የሚሉትን መምረጥ አትዘንጉ። ሁለቱን በአንድ ጊዜ በምታዙ ጊዜ የምትከፍሉት የአንዱን ብቻ መላኪያ ስለሆነ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ $7 ታተርፋላችሁ። በብዛት በቤተክርስቲያን ማዘዝ ለምትፈልጉ የዋጋ ቅናሽ ስላለን በኢሜል (fhlproduction@yahoo.com) ወይም በስልክ ቁጥር (403) 764-9184 ደውላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ። |
q ቁጥር ፩ ዲቪዲ ከተዘጋጀ በኋላ የተለያየ የዕድሜ ክልል ባላቸው በርካታ ልጆች ላይ ተሞክሮ የተገኘው ውጤት የሚያስደንቅ ነው። በጥናቱ የተካተቱት ልጆች በሙሉ የመጀመሪያ (ግዕዝ) ፊደላትን በሁለት ሳምንት ውስጥ ጠቅላላ የፈደል ዘሮችን ደግሞ በሦስት ወር አጠናቀው ሊያውቁ በቅተዋል።
|
q ቋንቋን ለልጆች ማውረስ አገርን ማውረስ ነው። አገር ማለት መልክዓምድሩ፣ በውስጡ ያለው ሀብትና አየር ንብረቱ ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ሕዝቡ ነው። አንድን ሕዝብ ከሌላው የሚለዩት ማንነቱ፣ እምነቱ፣ ባህሉ፣ ታሪኩና ቅርሱ ናቸው። ቋንቋን ማውረስ ይህን ባህል ማውረስ ነው። ቋንቋን ማውረስ እምነትን ማውረስ ነው። ቋንቋን ማውረስ ታሪክን ማውረስ ነው። ቋንቋን ማውረስ ማንነትን፣ ቅርስንና ሌሎችንም አገርን አገር የሚያደርጉትን እሴቶች ሁሉ ለልጆች ማውረስ ነው። እነዚህ እሴቶች የሌሉት ሰው የተሟላ ሊሆን አይችልም።
|


